የሀገር ውስጥ ዜና

በምስራቅ ሐረርጌ እና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ከ11 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን የንጹህ ውሃ ተጠቃሚ የሚያደርግ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ

By ዮሐንስ ደርበው

August 25, 2022

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በምስራቅ ሐረርጌ ዞን እና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የውሃ ምንጮች ላይ 11 ሺህ 700 ነዋሪዎችን የንጹህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ የሚያደርግ የውሃ መሳቢያ ተከላ ማካሄዱን አስታወቀ፡፡

በምስራቅ ሐረርጌ ዞን እና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ያለው የውሃ አቅርቦት በግጭት እና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት መስተጓጎሉን ኮሚቴው አስታውቋል፡፡