አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 19፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አሸባሪው ህወሓት መቀሌ ከሚገኘው የዓለም ምግብ ድርጅት መጋዘን ላይ የፈፀመው ዝርፊያ አስፀያፊ እና አሳፋሪ መሆኑን የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ባስሌ ተናገሩ።
የሽብር ቡድኑ ትናንት ጠዋት ላይ መቀሌ ወደሚገኘው የድርጅቱ መጋዘን በሀይል በመግባት 12 የነዳጅ ቦቴዎችን በአጠቃላይ 570 ሺህ ሊትር ነዳጅ መዝረፉን ተመድ መግለፁ ይታወቃል።
ይህን ድርጊቱን አስመልክተው ዋና ዳይሬክተሩ ባወጡት መግለጫ የህወሓት ድርጊት አስፀያፊና አሳፋሪ መሆኑን ገልፀዋል።
ነዳጅ ከሌለ በሚሊየን የሚቆጠሩ የሰብዓዊ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎችን መድረስ እንደማይቻል ነው የጠቆሙት።
በመሆኑም ቡድኑ የዘረፈውን ነዳጅ በአስቸኳይ እንዲመልስ አሳስበዋል።