Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ የተመራው ልዑክ ታላቁን የህዳሴ ግድብን ጎበኘ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ የተመራው ልዑክ ታላቁን የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብን ጎበኘ።

ልዑኩ የኡጋንዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ኦኬሎ ኦሪየም እና የሀገሪቱ የምድር ኃይል ዋና አዛዥና የፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የልዩ ዘመቻ ከፍተኛ አማካሪ ሌተናል ጀነራል ሙሆዚ ኪኑሩጋባን ጨምሮ የተለያዩ አባላትን ያካተተ ነው።

ለልዑካን ቡድኑ በግድቡ ዙሪያ ማብራሪያ ተሰጥቶታል።

ቀደም ሲል የልዑካን ቡድኑ በአዲስ አበባ የሚገኙትን የደኅንነት መሠረተ ልማቶች እና የቴክኖሎጂ ማዕከላትን ጎብኝቷል፡፡

የኡጋንዳ ከፍተኛ ባለስልጣናት የልዑካን ቡድን ባለፈው እሁድ ነበር ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ የገባው።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version