የሀገር ውስጥ ዜና

አንድ የሞሮኮ ኩባንያ ለኢትዮጵያ የማዳበሪያ ድጋፍ አደረገ

By ዮሐንስ ደርበው

August 24, 2022

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሞሮኮው የአፈር ማዳበሪያ አምራች ድርጅት (ኦ ሲ ፒ) የበጋ መስኖ ስንዴ ልማትን ለመደገፍ የሚውል የ50 ሺህ ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ ድጋፍ አደረገ፡፡

የኦ ሲ ፒ የአፍሪካ ዋና ስራ አስፈፃሚ መሀመድ አኑዋር ጀማሊ እንደገለጹት÷ ድርጅቱ ኢትዮጵያ የጀመረችውን በስንዴ ልማት ራስን የመቻል ራዕይ ለመደገፍ በማሰብ 50 ሺህ ሜትሪክ ቶን የአፈር ማዳበሪያ (ኤን ፒ ኤስ ቢ) ድጋፍ አድርጓል፡፡