አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 17፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) መንግሥት ለመድኃኒት አቅርቦት የተለየ ትኩረት በመስጠት ከፍተኛ በጀት መድቦ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ይናገር ደሴ ተናገሩ፡፡
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት አገልግሎት የ2014 ዓ.ም የህክምና ግብዓትና ክምችት ቆጠራ ሂደት ግምገማ መድረክ ተካሂዷል፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢና የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት አገልግሎት የቦርድ ሰብሳቢ ይናገር ደሴ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ መንግሥት ለመድኃኒት አቅርቦት የተለየ ትኩረት በመስጠት ከፍተኛ በጀት መድቦ አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
እንደ ሀገር በተለያዩ አካባቢዎች በተከሰቱ ችግሮች ምክንያት ጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ጋር በጋራ ከፍተኛ ተግባር መፈጸማቸውን አድንቀው÷ በቀጣይም በተጠናከረ ቅንጅት ተግባራትን ማከናወን ይገባል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ እንደገለጹት÷ ፈዋሽነታቸውና ደኅንነታቸው የተረጋገጡ መድኃኒቶችንና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን በበቂ መጠንና በተመጣጣኝ ዋጋ ለጤና ተቋማት በማቅረብ ረገድ አበረታች ውጤት ተመዝግቧል፡፡
ዘንድሮም የግዢ ሂደቶችን ቀልጣፋ በማድረግ፣ የጉድለት መጠንን በማሻሻል፣ የአቅርቦት ስርዓት ቁጥጥርን በማጠናከር በኩል ዘመናዊ አሠራሮችን መተግበራቸውን ተናግረዋል፡፡
በተለይ የህክምና ግብዓትና ክምችት ቆጠራ ሂደት የነበረበትን ክፍተት በማስቀረት አሁን ላይ ከፍተኛ ለውጥ ያስገኘ ተግባር እየተከናወነ ነው ማለታቸውን የጤና ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡
ታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!