የሀገር ውስጥ ዜና

የከፍተኛ ትምህርት አመራሮች ዓውደ ጥናት እየተካሔደ ነው

By Alemayehu Geremew

August 22, 2022

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አመራሮች የሁለት ቀናት የአመራር እና አስተዳደር ዓውደ ጥናት እየተካሄደ መሆኑ ተገለጸ፡፡

በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈፃሚ አምባሳደር ትሬሲ አን ጃኮብሰን ÷ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አመራሮች በተዘጋጀው ዓውደ ጥናት ላይ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል፡፡

አምባሳደር ጃኮብሰን በመልዕክታቸው፥ ዓውደ ጥናቱ የኢትዮጵያ እና የአሜሪካን ዩኒቨርሲቲዎች አጋርነት የሚያጠናክር ነው ብለዋል።

ዓውደ ጥናቱ በመሪነት፥ በሥራ አመራርና በአስተዳደር ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር እንደሆነም በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡