Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የፓኪስታን የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በሽብር ወንጀል ተከሰሱ

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የፓኪስታን ፖሊስ የሀገሪቷን የፀረ-ሽብር ኅግ በመጥቀስ የሀገሪቱን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካህን በሽብር ወንጀል መክሰሱ ተሰምቷል፡፡

የፓኪስታን ፖሊስ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኢምራን ካህን ላይ ምርመራ የጀመረው የሀገሪቷ ፖሊስ እና የፍትህ አካላት የቅርብ ረዳቶቼን በማሰር እና በማሰቃየት እያንገላቷቸው ነው በሚል ከከሰሷቸው በኋላ ነው ተብሏል።

ኢምራን ካህን የሀገሪቱ ፀረ ሽብር ህግ በመጣስ በከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ላይ ስጋት ደቅነዋል በሚልም ወንጅለዋቸዋል።

ክሱን ተከትሎም የኢምራን ካህን ደጋፊዎች በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ቤት አቅራቢያ መሰባሰባቸው ነው የተሰማው፡፡

በአሁኑ ጊዜም በሀገሪቷ ውጥረት የነገሰ ሲሆን ኢምራን ካህን የሚያዙ ከሆነ ደጋፊዎቻቸው ሥልጣኑን እንቆጣጠራለን በማለት እየዛቱ ነው ተብሏል፡፡

ኢምራን ካህን ሥልጣን ከለቀቁ ጀምሮ የፓኪስታንን መንግስትን እና ጦር በመተቸት ይታወቃሉ ሲል የዘገበው ቢቢሲ ነው፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version