የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከአንጎላ ጠቅላላ ምርጫ ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

August 21, 2022

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 15፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድንን የሚመሩት የቀድሞ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከአንጎላ ጠቅላላ ምርጫ ባለድርሻ አካላት ጋር ተወያይተዋል፡፡

አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በቅድመ ምርጫ ውይይታቸው የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮችን ጨምሮ ከተለያዩ ምርጫ አስፈጻሚ አካላት ጋር መክረዋል።