Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኦሮሚያ ክልል እና ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሻምፒዮን ሆኑ

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኦሮሚያ ክልል እና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ክልሎች እና ክለቦች ሻምፒዮን ሆነዋል፡፡

በክልሎች ሻምፒዮና መካከል በተደረገ የፍጻሜ ጨዋታ ኦሮሚያ ክልል ደቡብ ክልልን 2 ለ 0 በሆነ ውጤት መርታቱን ተከትሎ ሻምፒዮን ሆኗል፡፡

የማሸነፊያ ጎሎቹን ዮሴፍ ዳንኤል እና ጁንዲ ሃጂ ናቸው ያስቆጠሩት፡፡

እንዲሁም በክለቦች ሻምፒዮና መርሐ ግብር÷ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅዱስ ጊዮርጊስን በመለያ ምት 4 ለ 2 በመርታት የዋንጫ ባለቤትና ሻምፒዮን ሆኗል፡፡

በክለቦች ሻምፒዮና ዘርፍ በተካሄደው የሽልማት ሥነ ስርዓት÷ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወርቅ እና የዋንጫ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ የብር እንዲሁም ወላይታ ዲቻ የነሀስ እና የፀባይ ዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
በክልሎች ሻምፒዮና ደግሞ÷ ኦሮሚያ ክልል የወርቅ እና የዋንጫ፣ ደቡብ ክልል የብር እንዲሁም አማራ ክልል የነሀስ እና የፀባይ ዋንጫ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡
በተጨማሪም የኦሮሚያ ክልል ልዩ ተሸላሚ ሆኗል፡፡
ለአዘጋጁ ሲዳማ ክልል ደግሞ የዋንጫ ሽልማት ተበርክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

Exit mobile version