አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሊያ ርዕሰ መዲና ሞቃድሾ አልሸባብ በአንድ ሆቴል ላይ ጥቃት ፈፅሞ 10 ሰዎችን ገደለ።
የሽብር ቡድኑ ወደ ሆቴሉ ከመግባቱ በፊት በመግቢያው ላይ ሁለት ከባድ ፍንዳታዎችን አድርሷል።
በመቀጠልም ወደ ሆቴሉ ውስጣዊ ክፍል በመግባት የተኩስ እሩምታ በመክፈት 10 ሰዎችን ገድሏል።
በአልሸባብ ጥቃት ከሞቱት ሰዎች መካከል ስምንቱ ሲቪል መሆናቸው ነው የተገለፀው።
የመንግስት ልዩ ሀይል ወደ ሆቴሉ ዘልቆ በመግባት በውስጡ ይገኙ የነበሩ ሰዎችን ማስመለጥ ችሏል።
ይህ የመንግስት ልዩ ሀይል ሆቴሉን ከሽብር ቡድኑ አባላት ለማፅዳት ዘመቻውን መቀጠሉ የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል።