አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት እና ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ሙያተኞችን ለማሰልጠን የድጋፍ ሥምምነት ተፈራረሙ።
ሥምምነቱን የዩ ኤስ አይ ዲ ዳይሬክተር ሺን ጆንስ እና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ተሥፋዬ ሽፈራው (ዶ/ር) ተፈራርመዋል።
የድጋፍ ስምምነቱ 7 ነጥብ 7 ሚሊየን ዶላር ሲሆን፥ ድጋፉ ቀጣዩን ትውልድ በአደጋ ሥጋት አመራር ለማሠልጠን እና ባለሙያዎችን ለማፍራት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡
ቀደም ሲል በኢትዮጵያ የአሜሪካ ተራድዖ ድርጅት መዋዕለ-ንዋይ ዕውን የሆነው “ፊድ ዘ ፊውቸር ኢትዮጵያ” የተሰኘው መርሐ-ግብር ላለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሲተገበር መቆየቱን ዩ ኤስ ኤይድ በኢትዮጵያ በመረጃው አመላክቷል፡፡