Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኦሮሚያ የቱሪዝምና የቴክኖሎጂ ሳምንት ተከፈተ

 

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቴክኖሎጂን በመጠቀም የኦሮሚያን የቱሪስት መዳረሻዎች ማስተዋወቅ ላይ ያተኮረ የቱሪዝምና የቴክኖሎጂ ሳምንት ተከፈተ፡፡

በመክፈቻው ላይ የተገኙት የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ፥ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ የበለጸገች ሀገር ብትሆንም ከቱሪዝም ዘርፉ በሚገባት ልክ እንዳልተጠቀመች አንስተዋል።

ሀገሪቱ ከቱሪዝም ዘርፍ እንድትጠቀም ክልሉ የቱሪዝም ኮሚሽን በማቋቋም የኦሮሚያን የቱሪዝም መዳረሻዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ የተለያዩ ሥራዎች መሠራታቸውን ተናግረዋል፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትር ናሲሴ ጫሊ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ እምቅ የሆነ የቱሪዝም ሃብት ቢኖራትም በእውቀት የተመሰረተ ባለመሆኑ ሀገሪቱ ከዘርፉ መጠቀም እንዳልቻለች ተናግረዋል።

ከአምስቱ ዘርፎች መካከል አንዱ የሆነው የቱሪዝም ዘርፍን ከኢኮኖሚ ዘርፍ እኩል ቆጥሮ እየተሠራ መሆኑን አንስተዋል።

የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ኪሚሽነር ለሊሴ ዱጋ እንደገለጹት፥ በኦሮሚያ ክልል የቱሪዝም መዳረሻዎችን ለማስተዋወቅ በዘርፉ ላይ ወጣቶች ተደራጅተው የሥራ እድል እንዲፈጠር እየተሠራ ነው፡፡

የቱሪዝም እና የቴክኖሎጂ ሳምንቱ በስካይ ላይት ሆቴል ለአራት ቀናት ይቆያል፡፡

በቅድስት ብርሃኑ እና በለሊሲ ተስፋዬ

Exit mobile version