አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 3፣ 2014(ኤፍ ቢ ሲ) ጉዳዮችን ነቅሶ በማውጣት በውይይት እየፈቱ የጋራ ሀገር ለመገንባት ሁሉም ሚናውን መወጣት ይጠበቅበታል ሲሉ የሀገራዊ ምክክር ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ገለጹ።
በኮሚሽኑ ሀገራዊ ተልዕኮ ዙሪያ ግንዛቤ ማስጨበጥ ያለመ ውይይት አፋር ክልል ከፍተኛ አመራሮች፣ የሀገር ሽማግሌዎችና ወጣቶች ጋር ዛሬ በሠመራ ከተማ ተካሂዷል።
በውይይት መድረኩ ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ እንደተናገሩት ፥ ካለፉት ስድስት ወራት ወዲህ በኮሚሽኑ ዓላማና ተልዕኮ ዙሪያ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እየተደረገ ይገኛል።
የአፋር ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አወል አርባ በበኩላቸው ፥ ሁላችንም መኖር የምንችለው ሀገር ስትኖረን መሆኑ መታወቅ አለበት ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
የሚገጥሙ የሀሳብና አመለካከት ልዩነቶችን በሰለጠነ መንገድ በውይይት መፍታት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
የክልሉ መንግስትና ህዝብ ለኮሚሽኑ ሀገራዊ ተልዕኮ መሳካት የበኩሉን ሚና ለመጫወት ዝግጁ መሆኑን አንስተዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!