Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የ9 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ግምት ያለው ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚሆን የ9 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የአይነት ድጋፍ አስረክቧል፡፡

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ወ/ሮ አለሚቱ ኡመድ በድጋፍ ርክክቡ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ድጋፉ ከተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶችና ተቋማት መሰብሰቡን ጠቁመው÷ በገንዘብ ሲተመንም 9 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ግምት ያለው አልባሳት፣ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስና አልሚ ምግቦችን ያካተተ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ድጋፉን  የተረከቡት የኦሮሚያ ክልል የሴቶችና ሕጻናት ቢሮ አማካሪ ወ/ሮ ታሪኬ ሱባ በበኩላቸው÷ ድጋፉ በክልሉ በባሌ፣ ጉጂ፣ ቦረናና ሐረርጌ ዞኖች በሚገኙ ቆላማ አካባቢዎች በድርቅ ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች ይውላል ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

Exit mobile version