Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

10 ዞኖችና 6 ልዩ ወረዳዎች በክልል የመደራጀት ጥያቄአቸውን ለፌደሬሽን ምክር ቤት አቀረቡ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 28፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል የሚገኙ አሥር ዞኖችና ስድስት ልዩ ወረዳዎች በክልል የመደራጀት ጥያቄአቸውን ዛሬ ለፌደሬሽን ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡
ጥያቄውን የተቀበሉት የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ አገኘሁ ተሻገር÷ ምክር ቤቱ ውሳኔውን በአጭር ጊዜ ውስጥ ያሳውቃል ብለዋል።
ጥያቄውን ያቀረቡት የደቡብ ክልል የአሥሩ ዞኖች እና የሥድስቱ ልዩ ወረዳዎች ምክርቤቶች በክልል መደራጀታችን የህብረተሰቡን የልማት፣ የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች መፍታትና ኢትዮጵያዊ አብሮነትን ማጠናከር ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል።
በዙፋን ካሳሁን
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version