Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የሥኳር ሕመም ምልክቶች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 27፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሰዎች ሐኪም ዘንድ ከመቅረባቸው በፊት በሥኳር ሕመም ተይዘው ሊሆን እንደሚችል በሚያሳዩት ምልክቶች ቀድመው ሊገነዘቡ ይችላሉ፡፡

በተደጋጋሚ የሽንት መምጣት፣ ውሃ ጥም፣ ክብደት መቀነስ፣ ተደጋጋሚ የርሃብ ስሜት፣ ብዥ ያለ ዕይታ፣ የእጅ ወይም የእግር መደንዘዝ፣ ከፍተኛ የድካም ስሜት፣ የቆዳው ወዝ ማጣት እና መድረቅ፣

እንዲሁም መቁሰል የቁስሉ ቶሎ አለመዳን የሥኳር ሕመም ምልክቶች ስለሆኑ ሐኪም ዘንድ ሄደው ምርመራ ማድረግ ይኖርብዎታል፡፡

ዓይነት 1 እና ዓይነት 2 በመባል የተለዩ የሥኳር ሕመም ምልክቶች የተለዩ ሲሆን፥ የዓይነት 1 የሥኳር ሕመምተኞች የማቅለሽለሽ፣ የማስመለስ ወይም የሆድ ሕመም ሊኖራቸው ይችላል።

የዓይነት 1 የሥኳር ሕመም ብዙውን ጊዜ የሚጀምረው በልጅነት እና በጉርምስና ወቅት አንዳንድ ጊዜ ደግሞ በማንኛውም ዕድሜ ላይ ሊከሰት የሚችል ሲሆን ሕመምተኛው ሕመሙን አውቆ ክትትል ካላደረገ ወደ ከባድ ደረጃ ሊያመራ እንደሚችል የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከል ማዕከል በመረጃው አመላክቷል።

የዓይነት2 የሥኳር ሕመም ምልክት ከዕድሜ መጨመር ጋር ተያይዞ ሊከሰት ይችላል፡፡

ብዙውን ጊዜ በዓይነት 2 የሥኳር ሕመም የተያዙ ሰዎች ምንም ዓይነት የሕመም ምልክት ስለማያሳዩ ሳያስቡት አደገኛ ሁኔታ ላይ ሊወድቁ ይችላሉ፡፡

ስለሆነም በሕመሙ መያዙን በሐኪም ያረጋገጠ ሰው ክትትል ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን የዓለም አቀፉ የበሽታ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከል መረጃ ያመላክታል።

የስኳር ሕመም በእርጉዝ ሴቶች ላይ ምልክት ሳያሳይ ሊስተዋል ስለሚችል በእርግዝናቸው 24 እና 28ኛ ሣምንታት ሐኪማቸውን አማክረው መመርመር እና አስፈላጊውን ክትትል እና ምክር ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version