አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 22 ፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአልሻባብ ቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ኃላፊን ፏአድ መሐመድ ከሌፍ (ሼንጎሌ) ጨምሮ ሶስት የቡድኑ አመራሮች መደምሰሳቸውን የመከላከያ ኃይል ስምሪት ኃላፊና ጊዜያዊ የፀጥታ ኮማንድፖስት አስተባባሪ ሜጀር ጄኔራል ተስፋዬ አያሌው ተናገሩ።
ሜጀር ጀኔራል ተስፋዬ ለኢዜአ እንደተናገሩት ባለፉት ቀናት ከኢፌዴሪ አየር ኃይል ጋር በመቀናጀት በተወሰደው እርምጃ የሽብር ቡድኑ ኢትዮጵያን ለማጥቃት ያዘጋጃቸውን የትጥቅና ስንቅ ዴፖዎች ማውደም ተችሏል፡፡
በተጨማሪም የአሸባሪ ቡድኑ አመራሮችና ታጣቂዎች በተወሰደው እርምጃ ተደምስሰዋል።
ከተደመሰሱት ውስጥ የአልሸባብ ከፍተኛ ኮማንደሮች ውስጥ:-
1. ፏአድ መሐመድ ከለፍ (ሼንጎሌ) የአልሸባብ ቅስቀሳና ፕሮፓጋንዳ ሃላፊ፣
2.አብዱላዚዝ አቡ ሙሳ የአልሸባብ ቃል አቀባይ፣
3.ኡቤዳ ኑር ኢሴ የአልሸባብ የቦኮል ዞንና የኢትዮጵያ ድንበሮች አዋሳኝ ሃላፊ መደምሰሳቸውን ሜጀር ጄኔራል ተስፋዬ ለኢዜአ ገልጸዋል።