Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በ2015 በጀት ዓመት ለ16 አዳዲስ የመስኖ ፕሮጀክቶች ማስጀመሪያ 3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በጀት ተመደበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2015 በጀት ዓመት 16 አዳዲስ የመስኖ ፕሮጀክቶች እንደሚጀመሩ እና ለፕሮጀክቶች ማስጀመሪያ 3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በጀት መመደቡን የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

ለሚኒስቴሩ ለ2015 በጀት ዓመት 15 ነጥብ 16 ቢሊየን ብር የተመደበለት ሲሆን÷ ከመንግስት 11 ቢሊየን ብር ለፕሮጀክቶች ካፒታል በጀት እና 532 ሚሊየን ብር ለመደበኛ በጀት እንዲሁም 3 ነጥብ 63 ቢሊየን ብር ከዕርዳታና ብድር ተመድቧል ነው የተባለው፡፡

የተቋራጮች አቅም ማነስና የግብዓት አቅርቦት ችግርና የዋጋ መናር በ2014 በጀት ዓመት ያጋጠሙ ችግሮች መሆናቸውን የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሐመድ ገልጸዋል፡፡

ለመስኖ ፕሮጀክቶች ግብዓት እንዲሟላ ሰፊ ጥረት መደረጉን ጠቅሰው÷ በድርቅ የተጎዱ አካባቢዎችን በ19 ሚሊየን ዶላር የማቋቋም ሥራ ተሰርቷል ነው ያሉት፡፡

በ2015 በጀት ዓመት 16 አዳዲስ የመስኖ ፕሮጀክቶች እንደሚጀመሩ የተገለጸ ሲሆን÷ 10 የግንባታ እና 6 የጥናትና ዲዛይን ፕሮጀክቶች መሆናቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ መላክታል፡፡

ለፕሮጀክቶቹ 3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በጀት የተያዘላቸው ሲሆን÷ ቀሪው 7 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ደግሞ የነባር ፕሮጀክቶች በጀት ነው ተብሏል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

Exit mobile version