Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሻምፒዮናውን ኢትዮጵያ ከዓለም ሁለተኛ ሆና አጠናቀቀች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 18፣ 2014 (2014) የኦሪገንን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናን ኢትዮጵያ አራት የወርቅ፣ አራት የብር እና ሁለት የነሃስ ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከዓለም ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀቀች።

18ኛውን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በድምሩ 10 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከአፍሪካ በቀዳሚነት፣ ከዓለም ደግሞ ከአሜሪካ በመቀጠል 2ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

በሴቶች እና በወንዶች ማራቶች እንዲሁም በሴቶች 10 ሺህ እና 5 ሺህ ሜትር አራት የወርቅ ሜዳሊያዎችን በማግኘት ነው ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበችው።

ኢትዮጵያ በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል በሴት እና ወንድ እንዲሁም በወንዶች ማራቶን እና በሴቶች 1 ሺህ 500 ሜትር አራት የብር ሜዳሊያዎችን ስታገኝ፥ በሴቶች 3 ሺህ መሰናክል እና በሴቶች 5 ሺህ ሜትር ሁለት የነሐስ ሜዳሊያዎችን በአትሌቶቿ አግኝታለች።

ይህንንም ተከትሎ 18ኛውን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድርን ከአሜሪካ በመቀጠል ከዓለም ሁለተኛ ደረጃ፤ ከአፍሪካ ደግሞ አንደኛ ደረጃ ላይ በመሆን ጨርሳለች።

 

Exit mobile version