የሀገር ውስጥ ዜና

በአምራች ኢንተርፕራይዞች ዘርፍ በበጀት ዓመቱ ጥሩ አፈጻጸም ላሳዩ ክልሎች እውቅናና ሽልማት ተሰጠ

By Shambel Mihret

July 23, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 16፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት በ2014 በጀት ዓመት በዘርፉ የተሻለ አፈጻጸም ላሳዩ ክልሎች የእውቅናና ሽልማት መርሃ ግብር አካሂዷል፡፡

በተዘጋጀው መስፈርት መሰረት ከአንድ እስከ ሶስት ለወጡ የክልል የዘርፉ ቢሮዎች በኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ከፍተኛ አመራሮችና በአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ አመራር ሽልማት ተሰጥቷል::

በዚህም መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ አንደኛ የወጣ ሲሆን÷ የኦሮሚያ ክልል ስራ ዕድል ፈጠራና ክህሎት ቢሮ ሁለተኛ እንዲሁም የሲዳማ ክልል ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል::

በመድረኩ የአማራ ክልል ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ልዩ ተሸላሚ ሆኗል::

ክልሉ በጦርነት ሳይበገር ባለፉት 3 ወራት ያስመዘገበው ስራ የሚበረታታ መሆኑም መጠቆሙን ከኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!