Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አዲስ ወግ “ወጣቶች የነገዋ ኢትዮጵያ መሐንዲሶች” በሚል ርዕስ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬታሪያት የሚዘጋጀው ወርሀዊ አዲስ ወግ አንድ ጉዳይ የውይይት መድረክ “ወጣቶች የነገዋ ኢትዮጵያ መሐንዲሶች” በሚል ርዕስ ተካሂዷል።

ክፍለ ጊዜው ወጣቶች ለነገይቱ ኢትዮጵያ ያላቸውን አበርክቶት፣ ሚና እና ኃላፊነት የሚያመላክት ነው ተብሏል።

ወጣቶች ተግዳሮቶችን ተቋቁሞ በማሸነፍ ራሳቸውንም ሀገራቸውንም ለማሳደግ ያላቸውን እምቅ አቅም እንዲያስተውሉና እንዲጠቀሙበት ያሳስባል መባሉን ከጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version