Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በአንድ ጀምበር 7 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በአንድ ጀምበር 7 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 14፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 7 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኞችን የመትከል በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በአንድ ጀምበር 7 ነጥብ 5 ሚሊየን ችግኝ የመትከል መርሐ ግብር እየተካሄደ በሁሉም አካባቢዎች እየተካሄደ ነው፡፡

በዘመቻው የክልሉ ርዕሰ-መስተዳድር አቶ አሻድሊ ሀሰን፣ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ጽኅፈት ቤት ኃላፊ አቶ ይሥሃቅ አብዱልቃድር፣ የክልሉ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ ወይዘሮ ዓለምነሽ ይባስንን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የመንግስት ሠራተኞችና የክልሉ ሕዝብ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ፡፡

ርዕሰ-መስተዳድር አሻድሊ ሀሰን፣ በአብራሞ ወረዳ አፋ መንገሌ ቀበሌ ተገኝተው የማንጎ ክላስተር ላይ ችግኝ በመትከል አሻራቸውን አሳርፈዋል፡፡

በክልሉ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር 45 ሚሊየን ችግኞችን ለመትከል ታቅዷል፡፡

አቶ አሻድሊ ሀሰን በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ-ግብር በግላቸው 100 ችግኞችን ለመትከል ቃል-ገብተው ዐሻራቸውን እያሳረፉ እንደሚገኝ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version