Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ቻይና በ6 ሺህ ሜትር ጥልቀት ባሕር አሳሹን ሮቦት አስተዋወቀች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና በ6 ሺህ ሜትር ጥልቀት ባሕር ማሰስ የሚችለውን ሮቦት አስተዋውቃለች፡፡
ባሕር አሳሹ ሮቦት በርቀት መቆጣጠሪያ መሳሪያ የሚሠራ ሲሆን፥ ዌንሃይ -1 የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል።
በቻይናው የሳይንስ አካዳሚ አካል ሼንያንግ ኢንስቲቲዩት የተሠራው ሮቦት የተሳኩ 17 ሙከራዎችን ማድረጉ ተገልጿል፡፡
በዚህ ወቅት በባሕር ውስጥ በከፍተኛ ጥራት ከጎን የሚሰማ ድምፅ መለየት፣ በጥልቅ የባሕሩ ክፍል ውስጥ የሚገኝን ነገር መለየት፣ የነገሮችን ምንነት መለየት እና ልዩ ልዩ የናሙና ሥራዎችን የመሥራት አቅሙ መረጋገጡን ባለሙያዎች ተናግረዋል ።
ሮቦቱ በራሱ፣ በርቀት መቆጣጠሪያ እና ሁለቱን በማዋሃድ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን፥ ጠንከር ያሉ ሳይንሳዊ ሥራዎችን ቀለል ባለ ሁኔታ የማከናወን አቅም አለው ነው የተባለው።
በባሕር ሙከራው ወቅት በባሕር ዳርቻ አቅራቢያ ያለውን መረጃ የመለየት፣ የባሕር ወለል ንጣፍ እና የባሕር ወለል ባዮሎጂካል ናሙናዎችን መለየት መቻሉም ተጠቅሷል።
ከዚህ ባለፈም የምድር ስበት እና መግነጢሳዊ መስኮችን የለካ ሲሆን፥ ለባሕር ሃብት ፍለጋ እና ለዘርፈ ብዙ ተዛማጅ ምርምር የቴክኒክ ድጋፍ መስጠት እንደሚችል መገለጹን ሲ ጂ ቲ ኤን በዘገባው አመላክቷል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version