የሀገር ውስጥ ዜና

የአፍሪካን ችግሮች በአፍሪካውያን ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍ  በ3 የትምህርት ተቋማት መካከል ስምምነት ተደረገ

By Mikias Ayele

July 20, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ)የአፍሪካን ችግሮች በአፍሪካውያን ለመፍታት የሚደረገውን ጥረት በጥናትና ምርምር ለመደገፍ  በሶስት የአፍሪካ ሀገራት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መካከል ስምምነት ተደረገ።

ተቋማቱ ጥናትና ምርምሩን የሚያስተባብር የጋራ ግብረ-ሃይል ማቋቋማቸው ነው  የተገለጸው፡፡

ግብረ-ሃይሉን ያቋቋሙት የኢትዮጵያ፣ ዩጋንዳና ሩዋንዳ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሲሆኑ÷በአፍሪካ የሚከሰቱ ችግሮች በአፍሪካውያን እንዲፈቱ በጥናትና ምርምር የተደገፈ እገዛ ያደርጋሉ ተብሏል።

የጋራ ግብረ-ሃይሉን ያቋቋሙት ከኢትዮጵያ የጎንደር፣ ከዩጋንዳ የማኬሬሬ እና ከሩዋንዳ የኪጋሊ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትመሆናቸው ተመላክቷል፡፡

ተቀማጭነቱ ደቡብ አፍሪካ የሆነው ፎርት ሀሬ ዩኒቨርሲቲም የጋራ ግብረ-ሃይሉን ስራ እንደሚያስተባብር ተጠቁማል፡፡

ተቋማቱ ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔ ለመስጠት በጋራ እንደሚሰሩ ማስታወቃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡