ዓለምአቀፋዊ ዜና

ሶማሊላንድ ሉዓላዊነቴን ተጋፍቷል በሚል “ቢቢሲ”ን ከሥራ ማገዷተሰማ

By Alemayehu Geremew

July 20, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሶማሊላንድ ቢቢሲ የግዛቴን ሉዓላዊነት ተጋፍቷል በሚል ሥራውን እንዲያቆም መወሰኗን አስታወቀች፡፡

የሶማሊላንድ ማስታወቂያ ሚኒስትር ሳሌባን ዩሱፍ አሊ ኮሬ በሀርጌሳ በሰጡት መግለጫ ÷ ቢቢሲ ለ30 ዓመታት ራሷን ችላ ለቆመችው ዴሞክራሲያዊ ግዛት ዕውቅና አልሰጠም ብለዋል።

ከዛሬው ዕለት ጀምሮም ቢቢሲ በግዛቷ የሚሠራቸውን ሥራዎች እንዲያቆም መወሰኑን ነው የገለጹት፡፡

ሚኒስትሩ ÷ ጣቢያው የሚያሰራጫቸው መረጃዎች ለሶማሊላንድ ሕዝብ ጆሮ እንደማይመጥኑም አስገንዝበዋል፡፡

በፈረንጆቹ 1991 በሶማሊያ ተቀስቅሶ በነበረው የእርስ በርስ ጦርነት ሶማሊላንድ ከሶማሊያ ነጻ መሆኗን እንዳወጀች ዘ ኢስት አፍሪካን በዘገባው አስታውሷል ፡፡

ስለ እገዳው ከቢቢሲ የተሰጠ አስተያየት አለመኖሩ ተመላክቷል፡፡

ከእሲያ ሀገራት ውስጥም ቻይና ባሳለፍነው ዓመት ቢቢሲን ከስራ ማገዷ ይታወሳል፡፡