የሀገር ውስጥ ዜና

የአማራ ክልል በጎ ፈቃደኞች አገልግሎት መርሐ ግብር በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ተጀመረ

By Meseret Awoke

July 20, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢሲ) የዘንድሮው የአማራ ክልል በጎ ፈቃደኞች አገልግሎት መርሐ ግብር በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ በሚል መሪ ሃሳብ በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ባንጃ ወረዳ ተጀምሯል፡፡

በፕሮግራሙ የአማራ ክልል ርዕሰ መሥተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለን ጨምሮ የክልሉና የብሔረሰብ አስተዳደሩ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በመርሐ ግብሩ ላይ ወጣቶች በክረምቱ ወቅት አረጋውያንን በመንከባከብ፣ ሕጻናትን በትምሕርት በማገዝና በደም እጦት የሰው ሕይወት እንዳያልፍ ደም በመለገስ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ ማቅረባቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!