Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በተደጋጋሚ የሚያጋጥመውን የሰላም መደፍረስ ለመግታት መንግስት የማያዳግም እርምጃ ሊወስድ ይገባል – የአጣዬ ከተማ ነዋሪዎች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተደጋጋሚ የሚያጋጥመውን የሰላም መደፍረስ ለመግታት መንግስት የማያዳግም እርምጃ ሊወስድ ይገባል ሲሉ በሰሜን ሸዋ ዞን የአጣዬ ከተማ ነዋሪዎች ጠየቁ።
ነዋሪዎቹ ይህን ያሉት በይፋት ቀጠና የሰላምና ደህንነት ጉዳይ ላይ ትኩረቱን ያደረገ የምክክር መድረክ ዛሬ በአጣዬ ከተማ ሲካሄድ ነው።
ነዋሪዎቹ አሸባሪው ሸኔ በተደጋጋሚ በቀጠናው እያደረሰ ያለውን ጉዳት ለመቀልበስ መንግስት ህግ የማስከበር ዘመቻውን አጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ነው ያሉት።
አሸባሪውን ለመደምሰስ የሚደረገውን ጥረት ለመደገፍም ዝግጁ መሆናቸውን ነው የተናገሩት።
የአማራና የኦሮሞ ብሔረሰቦች በአብሮነት የኖሩ ናቸው ያሉት ነዋሪዎቹ አብሮነትን ለማዝለቅና ሰላምን ለማስከበር በጋራ መስራት እንደሚገባ ገልፀዋል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታደሰ ገብረ ፃድቅ ÷ ህግ የማስከበር ዘመቻው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አንስተዋል።
በሳምራዊት የስጋት
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version