የሀገር ውስጥ ዜና

የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽነሮች ከአቶ ርስቱ ይርዳ ጋር እየተወያዩ ነው

By Meseret Awoke

July 20, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 13፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የሀገራዊ የምክክር ኮሚሽነሮች ከደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ከአቶ ርስቱ ይርዳ እና ካቢኔ አባላት ጋር ውይይት እያካሔዱ ነው ፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ የኮሚሽኑ አባላት በህዝብ ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት፣ የግል ስብዕና እና ያላቸው የስራ ትጋት በቀጣይ ስለሚተገበሩ ሀገራዊ ጉዳዮች ህብረተሰቡ ተስፋ እንዲያደርግ ያስችላል ብለዋል።

ከሚሽነሮቹ በቀጣይ በሚከናወኑ ተግባራት ዝርዝር ጉዳዮች ዙሪያ ለርዕሰ መስተዳድሩ እና ለካቢኔ አባላት ገለጻ አድርገዋል።

የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ልሂቃን በሚያቀርቡት ሃሳብ ብቻ ችግሮች አይፈቱም ያሉት ኮሚሽነሮቹ ፥ ዜጎች በሀገራቸው ጉዳይ እኩል ተሳታፊ ሆነው የላቀ ድርሻ ማበርከት እንዳለባቸውም ጠቁመዋል።

የህብረተሰቡን ተሳትፎ በማሳደግ ረገድ የሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ ሊያደርጉ እንደሚገባም መናገራቸውን የደቡብ ክልል ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!