Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች በጉለሌ እፅዋት ማዕከል ችግኝ ተከሉ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 12፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ለአራተኛው ሀገር አቀፍ የአረንጓዴ ዐሻራ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ባዘጋጀው መርሐ ግብር ላይ ከተለያዩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ መገናኛ ብዙሃን የተውጣጡ ጋዜጠኞች በጉለሌ እፅዋት ማዕከል ችግኝ ተክለዋል።
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉ ጋዜጠኞች በሰጡት አስተያየት፥ ትክክለኛ መረጃን ለሕዝቡ ተደራሽ ከማድረግ ባለፈ እንዲህ ባለው ለትውልድ በሚሻገር ድርብ ሀገራዊ የዜግነት ኃላፊነት መወጣት ትርጉሙ ብዙ ነው ብለዋል።
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብሩ ባለፉት አራት ዓመታት በአካባቢ ጥበቃ ስራ ላይ ያመጣው ለውጥ ከፍተኛ እንደሆነ ያነሱት ጋዜጠኞችቹ÷ በቀጣይ ዓመታትም ከሀገር አልፎ በመላው ዓለም ተፅዕኖ መፍጠር በሚያስችል መልኩ ሁሉም ሰው ችግኞችን ሊተክል እና ሊንከባከብ እንደሚገባ ገለፀዋል።
የአረንጓዴ ዐሻራ ከፖለቲካ ጋር የማይገናኝ ለትውልድ የሚሻገር ፀጋ በመሆኑ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ጋዜጠኞች ግንዛቤ በመፍጠርና ለሕዝቡ ትክክለኛ መረጃ ተደራሽ በማድረግ ረገድ ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው ተብሏል።
በአዲሱ ሙሉነህ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version