የሀገር ውስጥ ዜና

ለተማሪ ኤፍሬም እናት በደሃ ተኮር ፕሮግራም ከተገነቡ ቤቶች ውስጥ ባለ ሁለት መኝታ ቤት ተበረከተ

By Meseret Awoke

July 18, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለተማሪ ኤፍሬም እናት በደሃ ተኮር ፕሮግራም ከተገነቡ ቤቶች ውስጥ ባለ ሁለት መኝታ ቤት አበረከተ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ፥ መማር እንደዚህ የሰው ልጆች አስተሳሰብ ላይ ለውጥ ሲያመጣ የተሟላ ትርጉም እንዳለው ገልጸዋል፡፡

በዚህም ተማሪ ኤፍሬም በለጠ የእናቱን ሸክም ሳያፍር ተሸክሞ የኢትዮጵያ እናቶችን ውጣውረድ ባደባባይ በማሳየቱ ምስጋና ይገባዋል ነው ያሉት።

ሌሎች ወጣቶችም በእናቶቻቸው ሸክምና ውጣ ውረድ የሚያፍሩ ሳይሆኑ፣ ተምረውና የአስተሳሰብ ለውጥ አምጥተው ከራሳቸውም አልፎ ሀገረን የሚለወጥ ራዕይ እንዲኖራቸው ለማነሳሳት ለተማሪ ኤፍሬም እናት በደሃ ተኮር ፕሮግራም ካስገነባናቸው ቤቶች ውስጥ ባለ ሁለት መኝታ ቤት አበርክተንላቸዋል ብለዋል ።

በተጨማሪም ማበረታቻ እንደተደረገላቸው የተገለጸ ሲሆን ፥ በቂርቆስ የምገባ ማዕከል የስራ ዕድል እንደተመቻቸላቸው ነው የተናገሩት።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!