Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር የጠበቀ ቅንጅት በመፍጠር በሀገራቱ ድንበር መካከል የታጠቁ ሃይሎች እንዳይንቀሳቀሱ እንደምትከላከል አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር የጠበቀ ቅንጅት በመፍጠር በሀገራቱ ድንበር መካከል የትኛውም የታጠቁ ሃይሎች እንዳይንቀሳቀሱ እንደምትከላከል የሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
 
የሱዳን መከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀኔራል ነቢል አብደላ በሰጡት መግለጫ፥በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል በድንበር አካባቢ ለተፈጠሩ ችግሮች አፋጣኝ እና ዘላቂ መፍትሄ ለማምጣት በሀገራቱ አመራሮች መካከል ውይይት መጀመሩን አስታውሰዋል፡፡
 
በተጀመረው የውይይት ማዕቀፍ ውስጥም ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር የጠበቀ ቅንጅት በመፍጠር በሀገራቱ ድንበር መካከል የትኛውም የታጠቁ ሃይሎች እንዳይንቀሳቀሱ እንደምትከላከል የሀገሪቱ የጸጥታው እና የመከላከያ ምክር ቤት የቴክኒክ ኮሚቴ ትናንት ባካሄደው ስብሰባ መወሰኑን አስታውቀዋል፡፡
 
ከዚህ ባለፈም ተዘግቶ የነበረው ሱዳንን በመተማ በኩል ከኢትዮጵያ ጋር የሚያገናኛት የገላባት ድንበር እንደገና እንዲከፈት መወሰኑን ነው የገለጹት፡፡
 
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version