ዓለምአቀፋዊ ዜና

በሶማሊያ ከደረሰ የአውሮፕላን አደጋ መንገደኞች ከጉዳት ተረፉ

By Mikias Ayele

July 18, 2022

አዲስ አበባ፣ ሀምሌ11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) 30 ሰዎችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረው የሶማሊያ መንገደኞች አውሮፕላን በሞቃዲሾ አውሮፕላን ማረፊያ መከስከሱ ተዘግቧል፡፡

የአውሮፕላን ማሪፊያው ባለስልጣናት እንደገለፁት፥ አውሮፕላኑ ሞቃዲሾ አየር ማረፊያ እያረፈ በነበረበት ወቅት አደጋ ደርሶበት በግዳጅ ያረፈ ሲሆን፥ በመንገደኞች ላይ ምንም ጉዳት አልደረሰም፡፡

አውሮፕላኑ ሞቃዲሾ አውሮፕላን ማረፊያ አካባቢ በኃይል ማረፉን ተከትሎ የእሳት ቃጠሎ መነሳቱንና አካባቢው በጭስ መሞላቱን ከስፍራው የወጡ ምስሎች ያሳያሉ፡፡

የጁባ ኤርዌይስ ንብረት የሆነው አውሮፕላኑ ከባይዶዋ ወደ ዋና ከተማዋ ሞቃዲሾ የውስጥ በረራ እያደረገ እንደነበርም ዋሽንግተን ፖስት ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!