Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የኬንያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በለተሰንበት ግደይ ላይ ያቀረበው ክስ ውድቅ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኬንያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በለተሰንበት ግደይ ላይ ያቀረበው ክስ ውድቅ ተደረገ።
በ10 ሺህ ሜትር ሴቶች በመጨረሻዎቹ ሰከንዶች ለተሰንበት ግደይ ሄለን ኦቢሪን በክርን መታታለች በሚል ኬንያ ለዓለም አቀፉ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቅሬታ አስገብቷል፡፡
ይሁን እንጅ ለተሰንበት ሄለንን በውድድሩ ፍፃሜ አካባቢ ቀድማት የነበረ በመሆኑንና አትሌቷ ዙሩን በበላይነት የማጠናቀቅ እድሏ ከፍተኛ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ክሱ ተቀባይነት ሳያገኝ መቅረቱን ከአፍሪካ ስፖርት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version