ዓለምአቀፋዊ ዜና

ሩሲያ ከዩክሬን ለሚከፈትባት ጥቃት ከባድ አፀፋዊ ምላሽ ትሰጣለች – ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ

By Alemayehu Geremew

July 18, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የቀድሞው የሩሲያ ፕሬዚዳንት ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ ዩክሬን ሀገራቸው ላይ ጥቃት ከከፈተች አፀፋዊ ምላሹ እጅግ የከፋ እንደሚሆን አስጠነቀቁ።

ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ አንዳንድ የዩክሬን ባለሥልጣናት ሩሲያን ለማስፈራራት በመገናኛ ብዙኃን መግለጫዎችን ሲሰጡ መታዘባቸውንና እና ድርጊታቸው የሚያስከትልባቸው መዘዝ እጅግ የከፋ እንደሚሆን መናገራቸውን አር ቲ ኒውስ ዘግቧል።

የዩክሬን የመከላከያ ሚኒስቴር የደኅንነት ክፍል ቃል አቀባይ ቫዲም ስኪቢትስኪ “በክሬሚያ ጥቁር ባሕር የሚገኙት የሩሲያ የጦር መርከቦች ለደኅንነታችን ስለሚያሰጉን በአሜሪካ-ሰራሽ ሮኬቶቻችን እንመታቸዋለን” ማለታቸው ይታወሳል።

ሜድቬዴም ዩክሬን ለምትፈጽመው ጥቃት ሞስኮ ከባድ አፀፋዊ መልስ ትሰጣለች ብለዋል።

ዲሚትሪ ሜድቬዴቭ ከፈረንጆቹ 2008 እስከ 2012 ሩሲያን በፕሬዚዳንትነት መምራታቸው ይታወሳል።

በአሁኑ ወቅት የሀገሪቱ የጸጥታ ምክር ቤት ምክትል ሊቀመንበር ሆነው እያገለገሉ ይገኛሉ።