የሀገር ውስጥ ዜና

የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ከ500 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር በላይ ገቢ አስመዘገበ

By Meseret Awoke

July 18, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2014 በጀት ዓመት ከአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ 500 ሚሊየን 44 ሺህ የአሜሪካን ዶላር መመዝገቡ ተገለጸ፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከክልሎች፣ የከተማ አሥተዳደር እና ተጠሪ ተቋማት ጋር በ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና በ 2015 በጀት ዓመት መነሻ ዕቅድ ላይ የተዘጋጀ የግምገማና የምክክር መድረክ በድሬዳዋ ከተማ እያካሄደ ነው።

የ2014 በጀት ዓመት ለኢንዱስትሪው መስክ ፈታኝ እንደነበር የገለጹት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል፥ የክልል፣ የከተማ አሥተዳደርና ተጠሪ ተቋማት ኢንዱስትሪ ቢሮዎች ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር ባደረጉት ቅንጅታዊ አሰራር የተሻለ ሥራዎች መስራት መቻሉን ጠቁመዋል።

በበጀት ዓመቱ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን በማነቃቃት፣ በሥራ ዕድል ፈጠራና ሥራ ያቆሙ ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ መልካም የሚባሉ ሥራዎች ተሠርተዋል ያሉት ሚኒስትሩ ፥ በዚህም ከዘርፉ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ መገኘት መቻሉን ተናግረዋል፡፡

በ2014 በጀት አመት ከአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ 500 ሚሊየን 44 ሺህ የአሜሪካን ዶላር መመዝገብ መቻሉንና ይህም ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ110 ሚሊየን ዶላር ብልጫ እንዳለው ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!