ስፓርት

በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ኡጋንዳ የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች

By Mekoya Hailemariam

July 18, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በ18ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በወንዶች 10 ሺህ ሜትር ኡጋንዳ የወርቅ ሜዳሊያ አገኘች።

ውድድሩን ኡጋንዳዊው አትሌት ጆሽዋ ቼፕቴጌ አሸንፏል።

እስከ ፍፃሜው ብርቱ ፉክክር ካደረጉት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች መካከል ሰለሞን ባረጋ አምስተኛ እና በሪሁ አረጋዊ ሰባተኛ በመሆን አጠናቀዋል።

ኬንያዊ እና ኡጋንዳዊ አትሌቶች በተከታታይ ሁለተኛና ሶስተኛ ሆነው ጨርሰዋል።