Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በአፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የተመራ የፓርላማና የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ልዑክ ጅግጅጋ ገባ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ አቶ ታገሰ ጫፎ የተመራ የፓርላማና የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ የአመራሮች ልዑክ ጅግጅጋ ገብቷል፡፡

ልዑኩ ገራድ ዊልዋል አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ÷ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡

የልዐኩ ጉዞ÷ በጅግጅጋ ከተማ እና በአካባቢዋ አረንጓዴ ዐሻራ ለማሳረፍ እንዲሁም የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ለማደስ ያለመ መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ለልዑካን ቡድኑ አባላትም የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሀመድ ስለ መርሐ ግብሩ ገለጻ አድርገዋል፡፡ ገለጻን ተከትሎም ውይይት ተካሂዷል፡፡

የሶማሌ ክልል ገና ሊለማ የሚችል 10 ነጥብ 5 ሚሊየን ሄክታር እንዳለው የገለጹት አቶ ሙስጠፌ÷ ዘንድሮ የታረሰው መሬት ቀደም ሲል ከሚታረሰው በእጥፍ እንደጨመረም አስረድተዋል።

የልዑካን ቡድኑ አባላትም÷ ክልሉ የያዘውን የልማት ጉዞ አድንቀው የግብርና ሥራውን ከሌሎች የልማት ተግባራቱ ጎን ለጎን አጠናክሮ ከቀጠለ ሀገር የመመገብ አቅም አለው ብለዋል፡፡

አረንጓዴ ዐሻራ የማኖሩ ሥራ እና የአቅመ ደካሞችን መኖሪያ ቤት የማደሱ ተግባራት ከነገ ጀምሮ እንደሚከናወንም ተመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version