Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ 2 ሺህ 881 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 881ተማሪዎች እያስመረቀ ነው፡፡
ተመራቂ ተማሪዎቹ በመደበኛ እና በማታ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኘት የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ፣ተመራቂ ተማሪዎች እና ቤተሰቦች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
ፕሮፌሰር ብርሀኑ ሀገራችን ከገጠማት ህመም ለመዳን ሁላችንም ሀላፊነት ቢኖርብንም የመምህራን እና የመምህራን ማሰልጠኛ ተቋማት ሚና ግን ድርብ ነው ብለዋል።
የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እና ብቁ ዜጋን ለማፍራት በቅድሚያ ብቁ መምህራንን ማፍራት ቁልፍ ጉዳይ ነው ብለዋል ሚኒስትሩ ።
ጥራት ያለውን ትውልድ ለማፍራት ጥራት ያላቸው መምህራንን ማፍራት እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡
ይህንን ለማድረግም በትምህርት ሚኒስቴር በኩል ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ ጠንካራ ስራዎች እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ብርሀነ መስቀል ጠና በበኩላቸው ÷ተመራቂዎች ሀገሪቱን ወደ ተሻለ የእድገት ጉዞ ለማሻገር ሚናቸውን እንዲወጡ መጠየቃቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version