Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ1ሺህ 500 ሜትር ማጣሪያዎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ወደ ቀጣይ ዙር አልፈዋል

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሬገን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለሊቱን በተካሄዱ የወንዶችና ሴቶች 1ሺህ 500 ሜትር ማጣሪያዎች በሴቶች ሁሉም ኢትዮጵያውያን ተወዳዳሪዎች አልፈዋል፡፡

ጉዳፍ ጸጋይ 4፡01.28 ከምድብ አንድ 1ኛ፣ ፍረወይኒ ኃይሉ 4፡02.28 ከምድብ አንድ 4ኛ፣ ሂሩት መሸሻ 4፡04.05 በሆነ ጊዜ ከምድብ ሁለት 2ኛ በመሆን አልፈዋል፡፡

በወንዶች ሳሙኤል ተፈራ (3፡36.35) እና ከፈጣኑ ምድብ ታደሰ ለሚ (3፡36.24) ወደ ግማሽ ፍጻሜ ሲያልፉ፥ ሳሙኤል ዘለቀ (3፡40.77) ሳያልፍ መቅረቱን ከአትሌቲክስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

Exit mobile version