የሀገር ውስጥ ዜና

ግሎባል አሊያንስ በመቅደላ ወረዳ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የምግብና የአልባሳት ድጋፍ አደረገ

By Meseret Awoke

July 16, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ግሎባል አሊያንስ በመቅደላ ወረዳ ለሚገኙ ተፈናቃዮች ከ3 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ በማድረግ የምግብና አልባሳት ድጋፍ አድርጓል፡፡

ጥምረቱ ከ2 ሺህ 500 በላይ ብርድ ልብስና 368 ኩንታል ዱቄት በወረዳው ለሚገኙ ተፈናቃዮች ድጋፍ አድርጓል።

የጥምረቱ አስተባባሪ አርቲስት ደሳለኝ ሀይሉ ጥምረቱ በበርካታ አካባቢዎች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ገልጾ ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግሯል፡፡

በድጋፉ ላይ የተገኙት የደቡብ ወሎ ዞን አስተዳዳሪ አቶ አብዱ ሁሴን በበኩላቸው ጥምረቱ ያደረገውን ድጋፍ አድንቀው በዞኑ በተለያዮ አካባቢዎች የሚገኙ ተፈናቃዮችን ለመደገፍ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ ነው ብለዋል፡፡

በከድር ሞሀመድ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!