Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የባንኮች አገልግሎት አሰጣጥ በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ መሆን አለበት – ዶክተር ይናገር ደሴ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የባንኮች አገልግሎት አሰጣጥ በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ መሆን እንዳለበት የብሔራዊ ባንክ ገዥ ዶክተር ይናገር ደሴ አሳሰቡ፡፡

10 ሺህ ያህል ባለአክሲዮኖች ያሉት አሐዱ ባንክ ዛሬ በይፋ ሥራውን ጀምሯል።

የብሔራዊ ባንክ ገዥ  ዶክትር ይናገር ደሴ ባንኩን በይፋ ሥራ ባስጀመሩበት ወቅት ባደረጉት ንግግር፥ የባንኮች አገልግሎት አሰጣጥ በቴክኖሎጂ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን አሳስበው፥  አሐዱ ባንክም ዘመናዊ  የቴክኖሎጂ አገልግሎቶች በመክፈቻው ዕለት በመተግበሩ አድንቀዋል፡፡

በኢትዮጵያ፥ ከፋይናንስ ተቋማት የብድር ተጠቃሚ ዜጎች ከ6 ሚሊየን  እንደማይበልጡ ጠቁመው፥ ባንኮች እና የቁጠባ ተቋማት በገጠሩ የሀገሪቱ ክፍል ለሚኖረው ማህበረሰብ የብድር አገልግሎት በማቅረብ ልማቱን መደገፍ  ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

አሐዱ ባንክ፥ በ564 ሚሊየን ብር የተከፈለ እና በ702 ሚሊየን ብር የተፈረመ ካፒታል ሥራውን መጀመሩም ተገልጿል፡፡

ባንኩ በዓመቱ ከሚያቀርበው ብድር 15 ከመቶ ያህሉን ለሥራ ፈጣሪዎች እና አንስተኛ ኢንተርፕራይዞች እንደሚያመቻችም ተመላክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

Exit mobile version