Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በ2014 በጀት ዓመት በአፋር ክልል ከ2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 9፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከ2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የአፋር ክልል ገቢዎች ቢሮ አስታወቀ፡፡

የቢሮው ኃላፊ አቶ መሀመድ ሀሰን እንደገለጹት÷ 2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 2 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ተሰብስቧል፡፡

የዕቅዱ 94 በመቶ መሳካቱን ጠቁመው÷ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸርም የ562 ሚሊየን ብር ብልጫ ማሳየቱን ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ክልሉ ገቢን በአግባቡ በመሰብሰብ የህብረተሰቡን የልማት ጥያቄ በተሻለ ሁኔታ ለመመለስ እየሠራ መሆኑንም ነው  የገለጹት፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

Exit mobile version