የሀገር ውስጥ ዜና

ፊቤላ ኢንዱስትሪያል ኮምፕሌክስ የሱፍ ዘይት አምርቶ ለገበያ ማቅረብ ጀመረ

By Meseret Awoke

July 15, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 8፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ፊቤላ ኢንዱስትሪያል ኮምፕሌክስ የሱፍ ዘይት አምርቶ ለገበያ ማቅረብ መጀመሩን አስታወቀ፡፡

ባለፈው አንድ ዓመት ከ95 ሚሊየን ሊትር በላይ የፓልም ዘይት አምርቶ ለገበያ አቅርቤያለሁ ያለው ድርጅቱ ፥ በአሁኑ ሠዓት የሱፍ ዘይት ማምረት ጀምሬያላሁ ብሏል።

በጥቂት ቀናት ውስጥ ብቻ ከአንድ ሚሊየን ሊትር በላይ የሱፍ ዘይት ማምረቱን የገለጸ ሲሆን ፥ ምርቱን ወደ ክልሎችም ማሠራጨት መጀመሩን ነው ያስታወቀው።

ፊቤላ ኢንዱስትሪያል ኮምፕሌክስ በሥሩ ባሉ ስምንት ያህል ፋብሪካዎች ዘይት ፣ ሣሙና ፣ የሣሙና ጥሪ እቃ ፣ የአትክልት ቅቤ፣ ሠሊጥ ፣ ፕላስቲክ ካርቶንና የከረጢት ማዳበሪያ እያመረተ እንደሚገኝ ከፌቤላ ኢንዱስትሪያል ኮምፕሌክስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!