Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የጣሊያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪዮ ድራጊ ሥልጣን ሊለቁ ነው

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) ጥምር መንግስት ለመመሥረት የሚያስችላቸውን የመተማመኛ ድምጽ ማጣታቸውን ተከትሎ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪዮ ድራጊ ከሥልጣናቸው እንደሚለቁ አስታውቀዋል፡፡

ማሪዮ ድራጊ የጣሊያንን ጥምር መንግስት ያቆየው መተማመናችን አብቅቶለታል ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ዛሬ ማምሻውን የሥራ መልቀቂያቸውን ለፕሬዚዳንቱ እንደሚያስከቡም ነው የተናገሩት።

ማሪዮ ድራጊ ባለፈው አመት በፕሬዚዳንት ማታሬላ በጠቅላይ ሚኒስትርነት መሾማቸው የሚታወስ ነው።

የአውሮፓ ኅብረት የኢኮኖሚ ቀውስ ሥር በመስደዱ እና ማሪዮ ድራጊ የሀገራቸውን የኑሮ ውድነት ለመቅረፍ በቂ ጥረት ባለማድረጋቸው ከቀድሞው የሀገሪቷ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ትችት እንደደረሰባቸው ብሎም ሥልጣናቸውን ለመልቀቅ ገፊ ምክንያት እንደሆናቸው ተመልክቷል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version