Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

በሶማሌ ክልል ከ25 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና እንደሚወስዱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በሶማሌ ክልል በዚህ ዓመት 25 ሺህ 145 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና በዩኒቨርሲቲዎች እንደሚሰጥ የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
የሶማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አብዱላሂ አደም ዩሱፍ እንደገለጹት÷ በዘንድሮው የትምህርት ዘመን በተለያዩ የክልሉ ትምህርት ቤቶች የ12ኛ ክፍል ትምህርታቸውን ላጠናቀቁ 25 ሺህ 145 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በክልሉ አካባቢዎች በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ይሰጣል፡፡
ፈተናው በዩኒቨርሲቲዎች እንዲሰጥ የተደረገው ኩረጃና አጭበርባሪነትን ለመከላከል መሆኑን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡
እስከ መስከረም 30 ቀን 2015 ዓ.ም ተፈታኝ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎች እንደሚጠሩ ጠቁመው÷ እያንዳንዱ ተማሪ በተመደበበት ዩኒቨርሲቲ እንዲገኝም አሳስበዋል፡፡’
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version