የሀገር ውስጥ ዜና

በ2014 በጀት ዓመት በኦሮሚያ ክልል ከልማት ድርጅቶች ከ100 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

By Mikias Ayele

July 14, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 7፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከልማት ድርጅቶቹ ከ100 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰብስቦ ለልማት ሥርዎች ማዋሉን አስታወቀ፡፡

በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመንግስት የልማት ተቋማት ክላስተር ዘርፍ አስተባባሪ ዶክተር ግርማ አመንቴ የዘርፉ የ2014 የሥራ አፈጻጸም ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው የክልሉ መንግስት ከመደበኛ እና ከማዘጋጃ ቤት 52 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር እንዲሁም ከበጎ ፍቃድ አገልግሎት 42 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡

ዶክተር ግርማ አመንቴ ÷ ክልሉ በበጀት ዓመቱ ለክላስተሩ ዘርፍ የመደበው 100 ነጥብ 38 ቢሊየን ብር በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋሉንም ነው የጠቆሙት።

አክለውም የክልሉ አፈጻጸም ምንም እንኳ በሀገሪቷ ችግሮች ቢያጋጥሙም በአጭር ጊዜ ውስጥ ብልፅግናን ዕውን ማድረግ እንደሚቻል ያሳየ ነው ብለዋል።

በኦሮሚያ ክልል ቀደም ሲል የተጓተቱና አዲስ የተጀመሩ ፕሮጀክቶች ከብር 10 ቢሊየን በላይ ወጪ ተደርጎባቸው መጠናቀቃቸውንም ገልጸዋል።

የክልሉ አብዛኛው በጀቱ ለካፒታል ፕሮጀክቶች ወጪ መደረጉንም ከኦሮሚያ ርዕሰ-መስተዳድር ጽኅፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡