Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ከእስራኤል አምባሳደር ጋር በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) አምባሳደር ብርቱካን አያኖ ከእስራኤል አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ጋር በሁለቱ ሀገራት መካከል የሚደረጉ አገልግሎቶች ቀልጣፋ እንዲሆኑ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱም÷ አምባሳደር ብርቱካን ኢትዮጵያ እና እስራኤል ረዥም ዘመን ያስቆጠረ ታሪካዊ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን ጠቅሰው ይህንን ወዳጅነትም የበለጠ ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።
አምባሳደር አለልኝ አድማሱ በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ እና በእስራኤል ሕዝቦች መካከል ያለው የጠበቀ ትስስር የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር መልካም እድል ይፈጥራል ማለታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
አምባሳደሮቹ የቆንስላ እና ዲፕሎማቲክ አገልግሎትን በሚመለከት ሀሳብ የተለዋወጡ ሲሆን÷ በሁለቱ ሀገራት መካከል የሚደረጉ አገልግሎቶች ቀልጣፋ እንዲሆኑ በሚቻልባቸው ጉዳይ ላይም ምክክር አድርገዋል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version