ቴክ

የአሊባባው አጋር አሊፔይ   የሞባይል የክፍያ መተግበሪያ አገልግሎቱን ሊያስፋፋ ነው

By Meseret Demissu

March 10, 2020

አዲስ አበባ፣መጋቢት 1፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የቻይናው የኤሌክትሮኒክስ ንግድ ኩባንያ አሊባባ አጋር አሊፔይ በመጪዎቹ 3 ዓመታት ውስጥ 40 ሚሊየን የአገልግሎት ፈላጊዎችን  የሞባይል ክፍያ መተግበሪያ ተጠቃሚ ለማድረግ መዘጋጀቱ ተገልጿል፡፡

በዚህ መተግበሪያ ተጠቃሚ  የሚሆኑ አገልግሎት ሰጪዎች 900 ሚሊየን ደንበኞቻቸው ጋር በቀላሉ ለመድረስ እንዲችሉ ያስችላል።

የአሊፔይ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሲሞን ሁ ÷ እርምጃው  ተቋሙ በባህላዊ መንገድ  ሲጠቀምበት የነበረውን የገንዘብ  አሠጣጥ አገልግሎት በመቀየር በኩል ከፍተኛ ድርሻ እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡

ከዚህ ባለፈ ዲጂታል የአኗኗር ዘይቤን መገንባቱ ለተጠቃሚዎቻች ከፍተኛ  ጥቅም ከማስገኘቱም በተጨማሪ  ኢንደስትሪውን በዲጂታል ለውጥ ለማፋጠንና ተጨማሪ የእድገት እድሎችን ለመክፈት ወሳኝ ሚና ይጫወታል  ብለዋል፡፡

ምንጭ፡-ሮይተርስ