Site icon Welcome to Fana Broadcasting Corporate S.C

የአውሮፓ ኅብረት – አባል ሀገራቱ በ’ስደተኞች ማዕበል’ሊጥለቀለቁ እንደሚችል ጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) በዩክሬን የዘለቀው ጦርነት ያባባሰው የምግብ አቅርቦት ዕጥረት ስደተኞች ወደ አውሮፓ ሀገራት እንዲያቀኑ ሊያስገድድ እንደሚችል የአውሮፓ የድንበር እና የባሕር ዳርቻ ጥበቃ ኤጀንሲ አስጠንቅቋል፡፡

የኤጀንሲው ዳይሬክተር አይጃ ካልናጃ ÷ የአውሮፓ ኅብረት ከዩክሬን የሚሰደዱትን ለመቀበል ዝግጁ መሆኑን ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

ጦርነቱ ዩክሬናውያንን ብቻ ሳይሆን ሰሜናዊ አፍሪካን ጨምሮ ከሀገሪቷ በወጪ ንግድ እህል ሲቀርብላቸው የነበሩ ሀገራትንም ጭምር ስለጎዳ ወደ አውሮፓ ሀገራት የሚተሙ ስደተኞች እንደሚኖሩ እና ለመቀበል መዘጋጀት እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

የዩክሬን ወቅታዊ ሁኔታ በፍጥነት ዕልባት ካላገኘ የስደተኞች ማዕበል ከሚያሰጋቸው ሀገራት ስፔን እና ጣልያን ግንባር ቀደም እንደሚሆኑ ኅብረቱ መጠቆሙን አር ቲ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
Exit mobile version