የሀገር ውስጥ ዜና

የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አመራሮችና ሠራተኞች የችግኝ ተከላ አካሄዱ

By Shambel Mihret

July 11, 2022

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 4፣ 2014 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አመራሮችና ሠራተኞች በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በጉለሌ እጽዋት ማዕከል የችግኝ ተከላ አካሂደዋል።

በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር አቶ ተፈሪ ፍቅሬና ሌሎች አመራሮች ተሳትፈዋል።

አቶ ተፈሪ÷ኢትዮጵያውያን በአረንጓዴ አሻራው የነቃ ተሳትፎ ሊያደርጉ እንደሚገባና ከችግኝ ተከላው ባሻገር ኢትዮጵያ በሁሉም መስክ እያደረገች ያለውን የለውጥ ጉዞ መደገፍ ይገባቸዋል ብለዋል።

የተተከሉችግኞችን በመንከባከብ ለታለመው ግብ መሳካት ሁሉም ኃላፊነቱን መወጣት አለበት ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!